ከኤድስ ነፃ የሆነች ኢትዮጵያ
ማን ነን
እ.ኤ.አ. በ2004 (በ1996ዓ.ም) በኤድስ ምክንያት የሚከሰት ሞት ኤችአይቪ በሃገራችን መከሰቱ ከታወቀበት እ.ኤ.አ 1986 አንስቶ ከታየው ሁሉ በላቀ ከፍተኛ መጠን ላይ ደርሶ ኤድስ ቁጥር አንድ የሞትና ህመም ምክንያት ወደመሆን ተሸጋግሮ የነበረ ሲሆን የሚስከትለው ቀውስ ዘርፈ ብዙና ውስብስብ መሆን በግልፅ የታየበት ነበር፡፡
ይህም የፖለቲካ አመራሮችን ቁርጠኛ የማስተባበርና መምራት አቅምንና ርብርብን የሚሻ መሆኑን በመረዳት በ1994 ዓ.ም ብሄራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ምክር ቤትና የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 276/1994፣ ሰኔ 1994 ዓ.ም ተቋቁመዋል፡፡
የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት ዓላማ የአገሪቱን የኤችአይቪ /ኤድስ ፖሊሲ አፈጻጸም ማስተባርና መምራት ሲሆን የሚከተሉት ኃላፊነቶችና ተግባራት አሉት፡፡
- የምክር ቤቱ ሴክሬታሪያት በመሆን ያገለግላል፣
- የምክር ቤቱን አስተያየት አካቶ የተዘጋጀ አገር አቀፍ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፕሮግራም ለመንግሰት አቅርቦ ያስፀድቃል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል ያስተባብራል፣
- ኤችአይቪ/ኤድስን ለመከላልና ለመቆጣጠር የሚንቀሳቀሱ የፌደራልና የክልል መንግስታዊ አካላትንና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን እንቅስቃሴ ያስተባብራል፣ የስራ ቅንጅት እንዲኖር ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣
- ኅብረተሰቡ ስለኤችአይቪ/ ኤድስ ግንዛቤ እንዲኖረው አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና አውደ ጥናቶች ያዘጋጃል እንዲዘጋጁም ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣
- በአገሪቱ ያለውን የኤችአይቪ/ኤድስ ገጽታ መረጃዎች ያሰባስባል፣ ያጠናቅራል፣ እንደአስፈላጊነቱ ለሚመለከታቸው ሁሉ ያሰራጫል፤
- ከተለያዩ ለጋሾች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ድጋፍ የሚገኝበትን ዘዴ ይቀይሳል፣
- በልገሳ የተገኘው ገንዘብና ከመንግስት የሚመደበው በጀት በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን ያረጋግጣል፣
|
የላቀ ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራሞችን ተቋማዊ በሆነ መልኩ እንዲተገበሩ በማድረግ፣ አገር አቀፍ የኤችአይቪ/ኤድስ ዘርፈ-ብዙ ምላሽን በማስተባበር፣ የጤና ሥርዓትንና የፕሮግራምና ማህበራዊ አስቻይ ሁኔታዎችን በማጠናከር በቀጣዮቹ ዓመታት የኤችአይቪ ቁጥጥር ግብን ማሳካት፣ |
አዲስ በኤችአይቪ የመያዝ መጠን እና በኤድስ ሳቢያ የሚከሰት የሞት መጠንን እኤአ በ2025 ወደ 1 ከ10,000 ሰዎች በታች በማውረድ በአገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጠውን የኤችአይቪ ቁጥጥር ግብ ማሳካት |
ዘርፈ ብዙ ምላሽ፡ እስካሁን በተገነባው አጋርነት ላይ በመመስረት የኤችአይቪ/ኤድስ ምላሹ የሁሉም ሴክተሮች/ተቋማትና የሁሉም አካላት ሃላፊነት ሆኖ ማስቀጠል |
እኤአ 2021-2025 የሚሸፍነው አገር አቀፍ የኤችአይቪ/ኢድስ ዘርፈብዙ ምላሽ ስትራቴጂክ እቅድ 6 ስትራቴጂክ አላማዎች ያስቀመጠ ሲሆን እነዚህም |