የመ/ቤት ዋና ዋና ተግባራት፤

የፌዴራል ኤችአይቪ/ኤድስ መከለከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አገራዊ የዘርፈ-ብዙ ኤችአይቪ/ኤድስ ምላሹን የሚያስተባብር መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡ አገራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽ በጤና ተቋማት የሚተገበሩ የኪሊኒካል ፕሮግራሞችን እና በማህበረሰብ ደረጃ የሚከናወኑ የዘርፈ-ብዙ ምላሽ ተግባራትን ያጠቃልላል፡፡ በዚህ ሁኔታ በአገርአቀፍ ደረጃ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፡፡

 • የዘርፈ-ብዙ ማስተባበር፣ አመራርና አጋርነትን ማጠናከር – አገራዊ የኤድስ ምክር ቤት፣ ሥራ አመራር ቦርድ፣ የተቀናጀ የጋራ ዕቅድና ግምገማዎችንና አጋርነት ፎረሞችን በመጠቀም አጠቃላይ አገራዊ የኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽ የማስተባበር፣ የአመራር ሚናን ማሳደግና ማቀናጀት ሥራዎች በጽ/ቤቱ ይከናወናሉ፡፡
 • መምራትና የአቅም ግንባታ ሥራዎች – አገራዊ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችን፣ መመሪያዎችን፣ ማንዋሎችና የተለያዩ ሰነዶችን በማዘጋጀት በስልጠና፣ በኦሬንተሸንና የልምድ ልውውጥ ሥራዎችን በማከናወን በኤችአይቪ ዙሪያ የሚሰሩ ሥራዎችን የመምራትና የአቅም ግንባታ ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡
 • ኤችአይቪ ቅድመ መከላከል – ይበልጥ ተጋላጭና ትኩረት የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎችን ኢላማ ያደረገ የባህሪ ለውጥ ተግባቦት፣ የማህበረሰብ ንቅናቄ፣ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት፣ የትምህርት ቤቶች ኤችአይቪ መከለከል እና በሥራ ቦታ ኤችአይቪ መከለከል ፕሮግራሞች በጥምር የኤችአይቪ መከላከል ሥራዎች ማለትም የባህሪያዊ፣ ባዮ-ሜዲካልና መዋቅራዊ መከላከል ሥራዎች አቀናጅቶ በያዘ መልክ ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡
 • የኤችአይቪ ሜይንስትሪሚንግ – በሁሉም ቁልፍ ሴክተሮች የኤችአይቪ ጉዳይ የዋና ተልዕኳቸው አካል ተደርጎና ተካቶ እንዲሰራ የማስተባበርና አቅም የመገንባት ሥራዎች ይሠራሉ፡፡
 • ድጋፍና ክብካቤ - በኤችአይቪ ምክንያት ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጫና የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎች የድጋፍና ክብካቤ አገልግሎቶች ተደራሽ እንዲሆኑ የልማት ድርጅቶችና ማህበረሰቡን በማስተባበር ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡
 • ለኤችአይቪ ምላሽ የሚውል ሀብት ማሰባሰብ – ከአገር ውስጥና ከውጭ ለጋሽ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ እንዲገኝ ማድረግ፣ የተገኘውን ገንዘብ ለፈጻሚና አስተባባሪ አካላት ማሰራጨትና በአግባቡ ሥራ ላይ መዋሉን ተከታትሎ የማረጋገጥ ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡
 • ክትትልና ግምገማ – የዘርፈ-ብዙ ምላሽ የክትትልና ግምገማ ሥርዓት መዘርጋት፣ አገራዊ የኤችአይቪ ስርጭት ሁኔታ መተንተንና ወቅታዊ ሪፖርቶችን ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ እንዲሁም የፕሮግራም አፈጻጸም ውጤታማነት የመዳሰስና መገምገም ሥራዎች ይከናወናሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የመረጃ ጥራት ማረጋገጥ ሥራዎችና የድጋፋዊ መስክ ምልከታ ተግባራዊ ይደረገጋሉ፡፡
አማርኛ

ለሕዝብ ይፋ የሚደረግ የጨረታ ግዥ ውድድር ውጤት ማስታወቂ ይዘት

የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ መንግስት [PEPFAR/CDC] ጋር ባለው የማዕቀፍ ስምምት መሠረት በሚደረግለት ድጋፍ ላለፉት አስርት አመታት የኤች/አይቪ ኤድስ ስርጭትን ለመቆጣጠር እና የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ ዘርፈ-ብዙ እንቅስቃሴዎች ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ አሁን ያለንበትን ሃገራዊ ብሎም ክልላዊ የኤች/አይቪ ኤድስ ስርጭት ስንመለከት እ.ኤ.አ በ 2020፣2025 እና 2030 የተቀመጡ ዓለማቀፋዊና አገራዊ ግቦችን ከማሳካት አንፃር ከፍተኛ ርብረብ የሚጠይቅ ነው፡፡ በመሆኑም አነዚህን ግቦች ላማሳካት ይረዱን ዘንድ የፌደራል የኤች/አይቪ ኤድስ መ/መ/ጽ/ቤት ከአሜሪካ መንግስት/ PEPFAR/CDC ባገኘው ድጋፍ የፀረ-ኤች/አይቪ መድሃኒትን በአግባቡ በመውሰድ እና የደም ውስጥ ያለውን ቫይረስ መጠንን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ በወሲብ አማካኝነት ያለን የመተላለፍ ሂደት መቀነስና መግታት ይቻላል ‘Undetectable equals Un-transmittable /U=U/’ የሚል ዘመቻ እና ማህበረሰባዊ ንቅናቄ ከ ጥቅምት 01/2013 ጀምሮ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ በደም ውስጥ ያለው ቫይረስ መጠንን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ለኤች/አይቪ ኤድስ ምርመራ፣ ህክምና እና የደም ውስጥ የቫይረስ ልኬት አገልግሎት ያለን ፍላጎት ከመጨመር፤ የጤና ባለሙያዎች ተነሳሽነት ከማሻሻል እና አድሎ እና መገለልን ከመከላከል አንፃር ፈርጀ ብዙ ጥቅም እንዳለው ይታመናል፡፡
ይህ ፕሮጀክት ከክልልና ከተማ አስተዳደሮች ጤና ቢሮዎችና ኤችአይቪ/ኤድስ መከ/መቆ/ጽ/ቤቶች፣ ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኙ ማህበራት፣ ጥምረቶችና ሌሎች አጋሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳሮች የሚተገበር ሲሆን የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

 • ለፕሮጀክቱ መነሻና መመሪያ የሚሆኑ ስትራቴጂዎችና ሰነዶችን ማዘጋጀት፣
 • የቫይረስ መጠን ልኬት ተጠቃሚነትን ለማሳደግ፣ የጸረ-ኤችአይቪ መድኃኒት ቁርኝት ለማጠናከርና የቫይረስ መራባት መጠን በሚፈለገው መጠን ማውረድን የሚመለከቱ መልዕክቶችን ማዘጋጀትና የተለያዩ የሚዲያ መንገዶችን በመጠቀም መልዕክት ማስተላለፍ፣
 • የቫይረስ መጠን ልኬት አገልግሎትና የመድኃኒት ቁርኝት ሥርዓት ማጠናከርና የአቅም ግንባታን ማከናወን
 • ጥምር የኤችአይቪ መከላከል ፕሮግራሞችን ማጠናከር፣

የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ሪፖርት