ኤችአይቪ/ኤድስ ስጋት እንዳይሆን፣ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ተገለጸ።

ግንቦት 18/2013 ዓ/ም ቢሾፍቱ: እ.ኤ.አ በ2030 ኤች አይ ቪ ኤድስ የሀገራችን ስጋት የማይሆንበት ደረጃ ላይ ለማድረስ በሚያስችል ደረጃ፣ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኘው የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት፣ እ.ኤ.አ ከ21-25 ሊተገበር የታቀደውን ስትራቴጂካዊ የዕቅድ ላይ ውይይት አድርጓል፡፡
የጽ/ቤቱ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እንደተገለጸው የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን በመግታት ረገድ፣ መዘናጋቱና ቸልተኝነቱ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንደሆነና በባለድርሻ አካላት እየተሰጠው ያለው ትኩረትም አናሳ እንደሆነ ተብራርቷል። ስርጭቱን ለመግታት፣ አመራሩ፣ ባለሙያው፣ ባለድርሻ አካላት፣ ከሃይማኖት ተቋማት እንዲሁም ህብረተሰቡ የሚጠበቅባቸውን ሚና መወጣት እንደሚገባቸው ተጠቁሟል። የተዘጋጀውን ዕቅድ በመረዳት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት መተግበር እንደሚገባና የሚጠበቀውን ውጤት ማስገኘት እንደሚገባ ተገልጿል።
በስትራቴጂክ ዕቅድ ውይይቱም ክልሎች፣ ከክልል ወረዳዎች የተውጣጡ የጤናና የኤች አይ ቪ ኤድስ ዘርፈ ብዙ ምላሽ ባለሙያዎች እንደተሳተፉ ታውቋል።

Undefined
የወጣበት ቀን: 
ሃሙስ, May 27, 2021
አስተዋውቅ: 
New Image: 

Add new comment