አዲሱ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ አስፈላጊነት

የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ በሽታ በዓለም ከተከሰተ ጀምሮ ሰዎችን በተለይም አምራች ኃይልን በማጥቃት ዘርፈ ብዙ የጤና፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚ እና ስነ-ህዝብ ችግሮችን ሲያስከትል የነበረ እና ያለ በሽታ ነው፡፡ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት እና ለመቆጣጠር በዓለም አቀፍ እና አገራት በተናጥል የተለያዩ ተግባራትን በመፈጸም ጥረት አድርገዋል፡፡ ኢትዮጵያ የኤች.አይ.ቪ ፖሊስን በ1990 ዓ.ም በማውጣት እና በ1994 በአዋጅ ቁጥር 276/94 የአገር አቀፍ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ምክር ቤት እና የኤች.አይ..ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት በማቋቋም ስርጭቱን ለመግታት ጥረት በማድረግ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል በተጨባጭ ለማሳየት ችላለች ያሉት የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ፀጋዬ ከተማ ሲሆኑ
የኤች.አይ.ቪ/ኤድሰ መከላከልና መቆጣጠር ተግባራት ከፍተኛ የሆነ ሀብት (ፋይናንስ) እና የባለብዙ ዘርፍ አካላት (multi-sectoral) ተሳትፎን የሚጠይቅ ነው፡፡ በመሆኑም አገራችን ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ከውጭ በሚገኝ ድጋፍ የተለያዩ ስራዎችን አከናውናለች፡፡ የአገሪቱ የህዝብ ቁጥር እና የበሽታው ተጋላጭነቱ በመጨመሩ በሽታውን የመከላከልና መቆጣጠር ተግባራት ወጪ ሲጨምር፤ በአንጻሩ ከውጭ ይገኝ የነበረው ድጋፍ ደግሞ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ በመሆኑ የችግሩ አሳሳቢነት ዳግም እየተከሰተ ባለበት በዚህ ወቅት ከውጭ ይገኝ የነበረው ድጋፍ እያሽቆለቆለ መገኘቱ አማራጭ የመፍትሄ መንገድ እንዲቀይስ ተቋማችንን የሚያስገድድ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
በመሆኑም ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ ከአገር ውስጥ ሀብት የማሰባሰብ እስትራቴጂ መከተል እና የባለብዙ ዘርፍ አካላት ተሳትፎን በአገር አቀፍ ደረጃ ማጠናከር አስፈላጊ ስለሆነ የፌዴራል ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ከሌሎች አካላት ጋር በመተባበር ከአገር ውስጥ ሀብት የማሰባሰብና ዘላቂ የማድረግ እስትራቴጂ አዘጋጅቷል፡፡ ሆኖም ለመተግበር እስትራቴጂው የያዛቸውን ቁልፍ ጉዳዮች ፤ አገር አቀፍ የባለብዙ ዘርፍ አካላት ተሳትፎ እና የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዋና ዋና ተግባራት በተመለከተ የተሟላ የህግ ማዕቀፍ እንዲኖር ማድረግ አንዱ አስፈላጊ ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም በሽታውን የመከላከልና የመቆጣጠር፣ በፌዴራል ደረጃ የሚያስተባብረውን አካል ኃላፊነትና አደረጃጀት እንዲሁም ከአገር ውስጥ ሀብት ስለሚሰበሰብበት ዋና ዋና ጉዳዮችን የያዘ አዋጅ ቁጥር 276/1994ን ሙሉ ለሙሉ የሚተካ ይህ ረቂቅ አዋጅ የተዘጋጀ ሲሆን ይህንንም ረቂቅ የማሻሻያ አዋጅ ለማጠናቀቅ ከፅ/ቤቱ አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መድረክ የተከናወነ ሲሆን በቀጣይ ስራውን ለማጠናቀቅ ጥረቶች በመደረግ ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

Undefined
የወጣበት ቀን: 
Monday, June 28, 2021
አስተዋውቅ: 
New Image: 

Add new comment