ጥቅምት 22/ 2014ዓ.ም. የማይታይ መጠን = የተገታ መተላለፍ ላይ የተሠሩ ስራዎችን በምን ሒደት ላይ እንዳሉ የሚያሳይ የግምገማ እና የስልጠና መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሄደ

በአገራችን የማይታይ መጠን የተገታ መተላለፍ ፕሮግራም/ COP20 / ከተጀመረ አንድ ዓመት አስቆጥሯል ። በመሆኑም አፈፃፀም ትግበራው ምን ይመስላል ? የሚለውን ለመቃኘት በተካሄደው የክትትል እና ግምገማ ወቅት የታዩ ክፍተቶችን ለሞምላት እና ክልሎችም የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ ይኼንን መድረክ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የCDC Ethiopia ምክትል ፕሮግራም ዳይሬክተር፣ ዶ/ር መናሽ ሻሃ የአምስት ዓመቱን አገር አቀፍ አቀፍ ስትራቴጂክ እቅድ አድንቀው፣የማይታይ መጠን የተገታ መተላለፍ ላይ የተከናወኑ ተግባራትም እንደ ጅምር ጥሩ እንቅስቃሴ የታየባቸው በመሆናቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
ከ600,000 በላይ የሚሆኑ ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች በኢትዮጵያ መኖራቸውን ያነሱት ምክትል የፕሮግራም ዳይሬክተሩ፣ በትክክል COP20 ን ፕሮግራም ተግባራዊ ከተደረገ ፤ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች በጤና ባለሙያዎች የታዘዘላቸውን የጸረ-ኤችአይቪ መድኃኒት በአግባቡ በመውሰድ፣ በደማቸው ውስጥ የቫይረስ መጠን የማይታይ መጠን ላይ ካደረሱ ፣ በግብረስጋ አማካኝነት የመተላለፍ እድሉ ስለሚገታ ጤናማ ኑሯቸውን ለመምራት ስለሚያስችላቸው ጠቀሜታው የጎላ ነው ብለዋል።
አቶ አብርሃም ገ/መድህን የፌደራል ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከ.መቆ. ፅ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር የመክፈቻ ንግግር ባቀረቡበት ወቅት አፅንዖት ሠጥተው እንዳነሱት፣ የ=የ መልዕክት ሲተላለፍ የመልዕክቱ ጭብጥ ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት እና የተለያዩ የሚዲያ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ፕሮግራሙን በደንብ ወደ ማህበረሰቡ ማስረፅ ያስፈልጋል ብለዋል።
በውይይት መድረኩ የማይታይ መጠን =የተገታ መተላለፍ ሠፊ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ፣ ይኼ ፕሮግራም በትክክል ተግባራዊ ከተደረገ፣ ኤች አይቪ ቀደማቸው ላሉ ወገኖች ጠቀሜታው የጎላ ከመሆኑም በላይ የመጀመሪያው 95 ግብን እንደሚያሳካ፤ የቫይረስ መጠን ልኬት ፍላጎት መጨመር እንደሚያስችል፣ የጸረ-ኤችአይቪ መድኃኒት ቁርኝትን እንደሚያሻሽል፣ የጤና ስርዓትን በማሻሻል ጥምር የኤችአይቪ መከላከል ሥራዎችን በከፍተኛ ደረጃ በማጠናከር እንደሀገር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተነስቷል፡፡

Undefined
የወጣበት ቀን: 
ሃሙስ, November 4, 2021
አስተዋውቅ: 
New Image: 

Add new comment