መርሆዎች

ዘርፈ ብዙ ምላሽ፡ እስካሁን በተገነባው አጋርነት ላይ በመመስረት የኤችአይቪ/ኤድስ ምላሹ የሁሉም ሴክተሮች/ተቋማትና የሁሉም አካላት ሃላፊነት ሆኖ ማስቀጠል
አካታችነት፡ የኤችአይቪ መከላከል ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች በተለያዩ የእድሜ ደረጃና የአኗናር ሁኔታ ያሉ ሰዎችን ማዕከል ያደረጉ ሆነው ሰዎች በሚያመቻቸው መልኩ መርጠው መጠቀም የሚችሏቸው እንዲሆኑ ማድረግ
ስርአተ ጾታን ያማከለ: የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር መረጃዎችና አገልግሎቶች ሴቶች፣ ወንዶች፣ ልጃገረዶችና ወጣት ወንዶች ከስርአተ ጾታ አንጻር ያላቸውን የተለያየ ፍላጎቶች ያገናዘቡና ምላሽ የሚሰጡ ማድረግ
ሃብት በአግባቡ መጠቀም /ስራ ላይ ለሚውል ሃብት ዋጋ መስጠት፡ በስትራቴጂክ እቅዱ የተካተቱ ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች በእቅድም ሆነ በትግበራ ወቅት የሚመደበውን ሃብት በአግባቡ ለመጠቀም ፍትሃዊነት፣ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ፣ ወጪ ቆጣቢነት፣ ውጤታማነት እና ቀጣይነትን ማረጋገጥ