ስትራጂክ ዓላማዎች

እኤአ 2021-2025 የሚሸፍነው አገር አቀፍ የኤችአይቪ/ኢድስ ዘርፈብዙ ምላሽ ስትራቴጂክ እቅድ 6 ስትራቴጂክ አላማዎች ያስቀመጠ ሲሆን እነዚህም
ስትራቴጂክ ዓላማ 1፡ እኤአ በ2025 90% የሚሆኑትን ለኤችአይቪ ስርጭት ቁልፍ የሆኑና ቅድሚያ የሚሰጣቸው/ ትኩረት የሚያሻቸው የማህበረሰብ ክፍሎችን በጥምር የኤችአይቪ መከላከል አገልግሎቶች ተደራሽ ማድረግ
ስትራቴጂክ ዓላማ 2፡ ኤችአይቪ ምርመራ አገልግሎትን በማጠናከር እኤአ በ2025 95% የሚሆኑት ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ተመርምረው ውጤታቸውን አንዲያውቁና አስፈላጊውን ህክምናና መድሃኒት እንዲያገኙ ማድረግ
ስትራቴጂክ ዓላማ 3፡ እኤአ በ2025 የኤችአይቪ እና ቂጥኝን ከእናት ወደልጅ መተላለፋቸውን መግታት
ስትራቴጂክ ዓላማ 4፡ እኤአ በ2025 95% የሚሆኑት ኤችአይቪ በደማቸው እንደሚገኝ ያወቁ ሰዎች የጸረ ኤችአይ ቪ መድሃኒት እንዲወስዱና መድሃኒቱን ከሚወስዱት ውስጥም 95% የሚሆኑት በደማቸው ያለው የቫይረስ ልኬት መጠን በሚፈለገው ደረጃ እንዲወርድ ማድረግ
ስትራቴጂክ ዓላማ 5፡ ለዘርፈብዙ ምላሹ ማስፈጸሚያ የሚሆን በቂ ሃብት ማሰባሰብና የተገኘውን ሃብት የላቀ ውጤታማነት በሚያመጣ መልኩ መደልደልና ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ
ስትራቴጂክ ዓላማ 6፡ መረጃ ላይ የተመረኮዘ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ ስትራቴጂክ መረጃዎችን ማመንጨትና ጥቅም ላይ የማዋል አሰራርን ማጠናከር