ፕሮጀክት

የኢትዮጵያ መንግስት ከአሜሪካ መንግስት [PEPFAR/CDC] ጋር ባለው የማዕቀፍ ስምምት መሠረት በሚደረግለት ድጋፍ ላለፉት አስርት አመታት የኤች/አይቪ ኤድስ ስርጭትን ለመቆጣጠር እና የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ ዘርፈ-ብዙ እንቅስቃሴዎች ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ አሁን ያለንበትን ሃገራዊ ብሎም ክልላዊ የኤች/አይቪ ኤድስ ስርጭት ስንመለከት እ.ኤ.አ በ 2020፣2025 እና 2030 የተቀመጡ ዓለማቀፋዊና አገራዊ ግቦችን ከማሳካት አንፃር ከፍተኛ ርብረብ የሚጠይቅ ነው፡፡ በመሆኑም አነዚህን ግቦች ላማሳካት ይረዱን ዘንድ የፌደራል የኤች/አይቪ ኤድስ መ/መ/ጽ/ቤት ከአሜሪካ መንግስት/ PEPFAR/CDC ባገኘው ድጋፍ የፀረ-ኤች/አይቪ መድሃኒትን በአግባቡ በመውሰድ እና የደም ውስጥ ያለውን ቫይረስ መጠንን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ በወሲብ አማካኝነት ያለን የመተላለፍ ሂደት መቀነስና መግታት ይቻላል ‘Undetectable equals Un-transmittable /U=U/’ የሚል ዘመቻ እና ማህበረሰባዊ ንቅናቄ ከ ጥቅምት 01/2013 ጀምሮ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ በደም ውስጥ ያለው ቫይረስ መጠንን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ለኤች/አይቪ ኤድስ ምርመራ፣ ህክምና እና የደም ውስጥ የቫይረስ ልኬት አገልግሎት ያለን ፍላጎት ከመጨመር፤ የጤና ባለሙያዎች ተነሳሽነት ከማሻሻል እና አድሎ እና መገለልን ከመከላከል አንፃር ፈርጀ ብዙ ጥቅም እንዳለው ይታመናል፡፡
ይህ ፕሮጀክት ከክልልና ከተማ አስተዳደሮች ጤና ቢሮዎችና ኤችአይቪ/ኤድስ መከ/መቆ/ጽ/ቤቶች፣ ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኙ ማህበራት፣ ጥምረቶችና ሌሎች አጋሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳሮች የሚተገበር ሲሆን የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

  • ለፕሮጀክቱ መነሻና መመሪያ የሚሆኑ ስትራቴጂዎችና ሰነዶችን ማዘጋጀት፣
  • የቫይረስ መጠን ልኬት ተጠቃሚነትን ለማሳደግ፣ የጸረ-ኤችአይቪ መድኃኒት ቁርኝት ለማጠናከርና የቫይረስ መራባት መጠን በሚፈለገው መጠን ማውረድን የሚመለከቱ መልዕክቶችን ማዘጋጀትና የተለያዩ የሚዲያ መንገዶችን በመጠቀም መልዕክት ማስተላለፍ፣
  • የቫይረስ መጠን ልኬት አገልግሎትና የመድኃኒት ቁርኝት ሥርዓት ማጠናከርና የአቅም ግንባታን ማከናወን
  • ጥምር የኤችአይቪ መከላከል ፕሮግራሞችን ማጠናከር፣