"ኤች አይቪ አሁንም ችግራችን ነው"

"ኤች አይቪ አሁንም ችግራችን ነው" በሀዋሳ የኢንዱስትሪ ፓርክ የኤችአይቪ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ። የፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ከሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጋር በትብብር ባዘጋጁት መድረክ ላይ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ድኤታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ "በአሁኑ ሰዓት በተገኘው ውጤት በመርካትና በመዘናጋት የባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች ተሳትፎና ርብርብ ቀንሷል። ባለን ውስን ሀብት ትክክለኛና በህብረተሰቡ ተቀባይነት ያለው የኤች አይቪ ኤድስ መረጃ ለህብረተሰቡ ማድረስ፤ ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖችና በኤድስ ምክንያት ያለአሳዳጊ የቀሩ ህጻናት ተገቢ ድጋፍ በማድረግ ሴቶች ወጣቶችና ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረገ ስራ መስራት ይጠይቃል።" ያሉ ሲሆን በመድረኩ ኤችአይቪ አሁንም ችግራችን ነው። ዛሬም በርካታ ወገኖች አዲስ በቫይረሱ ይያዛሉ ፣ ይሞታሉ። ወላጆች ዛሬም ልጆቻቸውን እንደ ትናንት በግልጽ ሊመክሩ ሊገስጹ፤ የሀይማኖት አባቶች የእምነት ልጆቻቸውን ሊያስተምሩ፤ ሚድያዎች ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ለህብረተሰቡ ግንዛቤ ሊፈጥሩ እንደሚገባ ተገልጿል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች በርካታ ወጣቶች ከቤተሰብ ተለይተው የሚገኙበት ቦታ ስለሆነ ለኤችአይቪ እንዳይጋለጡ አሰሪ ተቋማቱ ተደጋጋሚ የባህሪ ስልጠናዎችን ሊያመቻቹላቸው እንደሚገባ ተገልጿል።

Undefined
Posted on: 
Sunday, December 20, 2020
Alarm: 

Add new comment