Telephone: +25111-550-34-62/33 64
Fax number: +251-11-550-40-80
Postal Code: 122326
Address: Near Bambius super market
Afewerk Building, 6th ,7th, 8th Floor,
Addis Ababa, Sub city kirkos, wereda01,
Ethiopia
የፌደራል ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጣጠሪያ ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች የኮቪድ-19 ክትባት ወሰዱ፡፡
የጽ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብረሀም ገብረመድህን ክትባቱን መከተባቸውን ተከትሎ የተሰማቸውን ሲገልጹ “ብዙ የሚባሉ ብዥታዎች አሉ ግን ከሳይንስ ጋር መጣላት የለብኝም ይሄ ፈጣሪ ያመጣው ጸጋ ነው ብዬ ነው የማምነው መድሀኒት የሱ ስለሆነ ስሜቴ የእምነት ነው፤ ይሄ ክትባት መጀመሩ እራሱ የጥሩ ተስፋ ምልክት ነው፡፡”
ክትባቱን ከወሰዱ በኋላ አስተያየታቸውን የሰጡን የጽ/ቤቱ ሰራተኞች “ፊት የነበረውን ጭንቀት ከራስ በላይ ለቤተሰቤ ቫይረሱን ይዤ ቤተሰቤ ጋር መሄዴ ነበር የሚያሳስበኝ አሁን ግን ቢያንስ ቫይረሱን ይዤ ወደቤት አልሄድም ክብር ለሳይንስና ለተመራማሪዎች”
“ወረርሽኙን ለመግታት አስተዋጽኦ እንዳለው ስለማምን ደስተኛ ነኝ ነገር ግን አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል ስላልተከተበ ከመዘናጋት ይልቅ ለሌላውም በማሰብ ጥንቃቄያችንን አጠናክረን መቀጠል ይኖርብናል፤ ከግንዛቤ እጥረት የመከተብ አጋጣሚዎች ተፈጥረውላቸውም አልከተብም የሚሉ ስላሉ የተሻለ ግንዛቤ ቢፈጠርላቸው ጥሩ ነው፡፡”
ከዚህ ቀደም በጽህፈት ቤቱ የተወሰኑ ሰራተኞች እቤት ሆነው እንዲሰሩ መደረጉ እና እስካሁንም ለሰራተኛው የኮቪድ መከላከያ ቁሳቁስ እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡

Add new comment