የሚዲያ ንዑስ ፎረምን ማጠናከር ለኤች አይ ቪ መከላከል ስራው የጎላ ሚና እንዳለው ተገለፀ

ግንቦት 02/2013 ዓ/ም አዳማ:-አቶ አብርሃም ገ/መድህን የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር በፌደራል ለሚገኙ ከግል እና ከመንግስት ሚዲያዎች ለተውጣጡ የሚዲያ አካላት ፣ የሚዲያ ፎረሙን በባለቤትነት ስሜት ለማጠናከር የሚዲያው ተሳትፎ እና ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ የውይይት መድረኩን በከፈቱበት ወቅት የገለፁ ሲሆን፤ የኤች አይቪ/ኤድስ ስርጭትን ለመግታትና ስለ ቫይረሱ ምንነት፣ እያስከተለ ስላለው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተፅዕኖን የሚያስገነዝቡ ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ለሚዲያው ማህበራዊ ኃላፊነትን ከመወጣት አንፃር የሚጠበቅ ተግባር መሆኑንም አንስተዋል።
አቶ ነፃነት ሐኒቆ የፌደራል ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከ.መቆ. ፅ/ቤት የእቅድ ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከ2014-2018 ዓ.ም ተግባራዊ የሚሆነው ስትራቴጂክ እቅድ ለሚዲያ አካላት መረጃ አሠጣጥ ተደራሽ በሚሆን መልኩ ያቀረቡ ሲሆን፤ አዲሱ ስትራቴጂክ እቅድ ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ የስርጭት ምጣኔው ከፍተኛ የሆነበትን አካባቢና ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦችን በመለየትና እንደ አካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ፣ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ ፍትሐዊ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህንን ወደ ተግባር መቀየር የሁሉም የቤት ስራ ሊሆን እንደሚገባም ተወሰቷል ።
በእለቱ ከCDC/Ethiopia የመጡት አቶ ዮናታን አለሙ ለሚዲያ ፎረሙ ተሳታፊዎች ስለ ጤና አዘጋገብ ስልት እና ትኩረት ሊደረግባቸው ስለሚገባቸው መሠረታዊ የጋዜጠኝነት መርሆዎችን ከጤና ዘገባ ጋር በምሳሌ እያስደገፉ ለግማሽ ቀን ስልጠና ሰጥተዋል።
በተጨማሪም የሚዲያ አካላት ለኤች አይ ቪ መከላከሉ ስራ ማህበረሰብ ላይ የአድቮኬሲ ስራ በመስራት የተሻለ ለውጥ እንደሚያመጡ ነባራዊ ሁነቶችን እንደ ምሳሌ እያጣቀሱ ያሳዩ ሲሆን፤ ያለ መገናኛ ብዙሃን ተሳትፎ የኤች አይ ቪ መከላከል ስራው ስኬታማ እንደማይሆን በመገንዘብ የሚዲያ ፎረሙን በማጠናከር እንዲሁም ከስራቸው ጎን ለጎን ማህበረሰቡ ስለ ኤች አይ ቪ ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ አጋር እንዲሆኑ ጠይቀዋል።

Undefined
Posted on: 
Wednesday, May 12, 2021
Alarm: 

Add new comment