ስርዓተ ጾታ እና የኤችአይቪ ምላሽን ያካተተ የዳሰሳ ጥናት ይፋ ተደረገ።

ሰኔ 7/2013 ዓ/ም; አዳማ: የፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጽጌረዳ ክፍሌ የዳሰሳ ጥናቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት እንደተናገሩት በሀገራችን ልጃገረዶችና ሴቶች በትምህርት፣ በጤና አገልግሎት፣ በመሰረታዊ የኑሮ ፍላጎትና ሰብአዊ መብት ጉዳዮች ከአጠቃላይ ማህበረሰቡ ጋር ሲነጻጸር የተጎዱ መሆናቸውን በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩ አውስተው መንግስት የስርዓተ ፆታ እኩልነትን ለማረጋገጥ ከህገ መንግስት ጀምሮ ጠንካራ የሴቶች ፖሊሲ በማውጣትና እንዲተገበሩ በማድረግ ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደተቻለ ገልጸዋል። ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም የፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባር መሰረት በማድረግ ይህ የዳሰሳ ጥናት እንዲከናወን ያደረገ እንደሆነና በጥናቱ የተገኙ መረጃዎችን በመተንተን ኤች አይቪ የማህበረሰብ የጤና ችግር እንዳይሆን በሚተገበረው ዘርፈ ብዙ ምላሽ ላይ በሚከናወኑ ተግባራት ባለድርሻ አካለት ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የእናቶች፣ የህፃናትና ወጣቶች ተ/ ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ልጅዓለም እንደገለጹት ላለፉት አስር ወራት በተከናወነው የዳሰሳ ጥናት የተለያዩ ውጤቶች እንደተገኙ ገልጸው የኤች አይቪ ስርጭት ምጣኔ ከስርዓተ ፆታ የፍትሐዊነት ችግር ፣ የኤች አይቪ ምላሽ ስርዓተ ፆታን በሚፈለገው ልክ ያላካተተ እንደሆነ በተጨማሪም የስርዓተ ፆታ ጉዳዮችን ተደራሽ ለማድረግ የተመደመ በጀት በግልጽ አለመታወቁ በዳሰሳው ወቅት ከተገኙ ዉጤቶች መካከል እንደሆኑ አንስተው የተገኘው የዳሰሳ ውጤትን መሰርት በማድረግ በቀጣይ የተለያዩ ተግባራት መከናወን እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
የዳሰሳ ጥናቱ ከUNAIDS በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተከናወነ እንደሆነና የዳሰሳ ጥናቱ በሰነድ እንዲዘጋጅ UNWOMEN ድጋፍ እንዳደረገ ተገልጿል።
የዳሰሳ ጥናቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት ከጤና ሚኒስቴር፣ ከፌደራል ኤችአይቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት፣ ከፌደራል የሴቶችና ህፃናት ወጣቶች ሚኒስቴር፣ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

Undefined
Posted on: 
Monday, June 14, 2021
Alarm: 
New Image: 

Add new comment