Telephone: +25111-550-34-62/33 64
Fax number: +251-11-550-40-80
Postal Code: 122326
Address: Near Bambius super market
Afewerk Building, 6th ,7th, 8th Floor,
Addis Ababa, Sub city kirkos, wereda01,
Ethiopia
የኤች አይቪ/ኤድስ ዘርፈ ብዙ ምላሽ የ2013 በጀት ዓመት አፈፃፀምም ማጠቃለያ ሪፖርት እና የ2014 በጀት ዓመት አንኳር መነሻ እቅድ ዝግጅት መድረክ በዓዳማ ከተማ ድሬ ኢንተርናሽናል ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል
የፌደራል ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት ከክልል ጤና ቢሮ እና ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከ.መቆ. ፅ/ቤት ከተውጣጡ የዕቅድ ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እና ዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስተባበር የፕሮግራም አስተባባሪዎች፣ እንዲሁም ከፌደራል ጥሪ ለተደረገላቸው ሴክተር መ/ቤት ጋር በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ አንኳር አገር አቀፍ የኤች አይ ቪ/ኤድስ እቅድ ክንውኖችን በመገምገም ላይ ይገኛል።
የፌደራል ኤች አይ ቪ ኤድስ መከ.መቆ. ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፅጌረዳ ክፍሌ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት እንደገለፁት 2013 ዓ.ም. ቀደም ሲል የነበረውን እስትራቴጂክ ዕቅድ ያጠናቀቅንበት እና አዲሱን እስትራቴጂክ ዕቅድ የተቀበልንበት ዓመት መሆኑን አስታውሰው አሁን ላይ የኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት ምጣኔ እንደሀገር እየቀነሠ ቢሆንም ከክልል ክልል የስርጭት ምጣኔው ከፍተኛ ልዩነት እንዳለው ገልፀዋል። አክለውም ኤች አይ ቪ የጤናው ሴክተር ስራ ብቻ ሳይሆን የሁሉንም አካላት ሁለንተናዊ ተሳትፎ ስለሚጠይቅ በቀጣይ አምስት ዓመት አዲሱን እስትራቴጂክ ዕቅድ በተገቢው መንገድ ለመተግበር የተሰሩ ጥናቶችን መሠረት አድርገን ሶስቱን 95 ለማሳካት የሚያስችለንን ስራ ለመስራት የሁላችንንም ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅ ገልፀው፤ አዳዲስ የኤች አይ ቪ መከላከል ስልቶችን ለህብረተሰቡ በተገቢው መንገድ ተደራሽ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ነጋሽ ስሜ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደተናገሩት ኤች አይቪ የአንድ ተቋም ብቻ ስላልሆነ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በ2030 እንደርስበታለን ብለን አንግበን የተነሳነውን ራዕይ ለማሳካት በጋራ መስራት ይጠበቅብናል በማለት አፅንዖት ሰጥተው ገልፀዋል።
አቶ ነፃነት ሐኒቆ የፌደራል ኤች አይቪ/ኤድስ መከ.መቆ.ፅ/ቤት የዕቅድ ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክተር የ ኤች አይ ቪ ዘርፈ ብዙ ምላሹን የ2013በጀት ዓመት አፈፃፀምም ማጠቃለያ ሪፖርት እና የ2014 በጀት ዓመት አንኳር መነሻ እቅድን አቅርበዋል።


Add new comment