የፌደራል ኤች አይ ቪ/ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት ለተቋሙ አጠቃላይ ሰራተኞች የ=የ የማይታይ መጠን = የተገታ መተላለፍ ላይ እንዲሁም የስራ ቦታ ትንኮሳ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

በደሙ ውስጥ ኤችአይቪ የሚገኝበት ሠው የፀረ-ኤች አይ ቪ ህክምና በአግባቡ እየወሠደ፣ በደሙ ውስጥ ያለውን የቫይረስ መጠን ልኬት ቢያንስ ለሁለት ጊዜያት ወቅቱን ጠብቆ አሰርቶ ቫይረሱ የማይታይ መጠን ላይ ከደረሠ፤ በግብረ- ስጋ ግንኙነት አማካኝነት የሚተላለፍ የኤች አይ ቪ ስርጭትን ለመግታት የሚያስችል አዲስ የኤች አይቪ መከላከል ፕሮግራም እንደሆነ ተገልጿል።
በእለቱ ስልጠናውን የሠጡት የዕቅድ ክትትል እና ግምገማ ዳይሮክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ቢኒያም እንደገለፁት፦ ይህ አዲስ ፕሮግራም በዓለም ላይ ከ100 በላይ አገሮች በላይ እየተገበሩት እንደሆነ ፤ CDC PEPFAR ይኼንን ፕሮግራም የተለያዩ የግንዛቤ መፍጠሪያ መሳሪያዎችን በመጠቀም ንቅናቄውን ካስጀመረ አንድ ዓመት ሊሞላው በጣት የሚቆጠሩ ቀናት እንደቀረውም በመድረኩ ላይ ተገልጿል። በተጨማሪም ይሄንን ፕሮግራም ወደ ማህበረሰቡ በደንብ ተደራሽ ለማድረግ የጤና ባለሙያዎች እና የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች በቅንጅት እየሠሩ እንደሆነ ተናግረዋል።
በጤና ሚኒስትር የሴቶች እና ወጣቶች ባለሞያ የሆኑት አቶ አቤል ሞሴ እንደገለፁት፣ ከስራ ቦታ ጋር በተያያዘ ያሉ ትንኮሳዎች ምን ይመስላሉ? በስራ ቦታ ላይ ፆታዊ ጥቃት ቢያጋጥም የአገራችን የህግ ማዕቀፍ የሚሰጠውምላሽ ምን ይመስላል? የሚለውን አዋጅ ቁ.1064/2017.አንቀፅ2(13) ጠቅሠው አስረድተዋል።
በተጨማሪም የጤናው ዘርፍ ለሶስተኛ ጊዜ ያሻሻለውን የስርዓተ ፆታ ማካተቻ ማንዋል ላይ አጭር ገለፃ ሰጥተዋል።

Undefined
Posted on: 
Wednesday, September 29, 2021
Alarm: 
New Image: