ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጡ

11/02/2014 አዳማ፡- የፌደራል ኤችአይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የ2014 አመታዊ የስራ ግምገማ መድረክ ላይ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታ የሆኑት ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በመድረኩ ላይ በመገኘት ከተለያዩ ክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ መስተዳድሮች ጋር በመወያየት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጡ፡፡
በኤችአይ ቪ ኤድስ ላይ እስከዛሬ በተሰሩት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ማህበረሰቡ ላይ የመጣውን ከፍተኛ የግንዛቤ ለውጥ ተመልክተናል ታዲያ ኤችአይ ቪ ሰፊ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄ ዛሬም የሚፈልግ መሆኑን የገለፁት ሚኒስቴር ዴኤታው ክልሎች ኤችአይ ቪን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እየሰሩት ያለው ስራ ምን እንደሚመስል የነበራቸው ጥንካሬ እንዲሁም ያጋጠማቸው ችግር ምን እነደሆነ እና ከፌደራል ኤችአይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት እና ከጤና ሚኒስቴር እንዲደረግላቸው ስለሚጠብቁት ድጋፍ እና እገዛ በስፋት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይተውበታል፡፡
በከፍተኛ ደረጃ የሁሉም ክልሎች ጥያቄ እየሆነ ያለው በኤችአይ ቪ ኣዳዲስ የሚያዙ ሰዎችን ለመቀነስ ከፍተኛ ሚና የሚጫወተውን የኮንዶም አቅርቦት ከፍተኛ የሆነ ችግር መሆኑ የተስተዋለ ሲሆን ችግሩ በከፍተኛ ሁኔታ በባለፉት አመታትም ችግር ሆኖብን ቆይቶአል በተለያየ መልኩ ለመፍታት ተሞክሮአል ነገር ግን የጥራት ጉዳይ ወደሃላ እያረገን ይገኛል በተጨማሪም የክልሎችም የኮንዶም አጠቃቀምም መታየት ያለበት ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው ከከፍተኛ አመራሮች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ችግሩን ለመፍታት እንሰራለን ሲሉ ሚኒስቴር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡

Undefined
Posted on: 
Friday, October 22, 2021
Alarm: 
New Image: