ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ

የፌደራል ኤችአይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት 33ኛውን የአለም ኤድስ ቀን አከባበር ላይያተኮረ ጋዜጣዊ መግለጫ ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ለተወጣጡ ጋዜጠኞች በጽ/ቤቱ ሰጠ፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ ለ33ኛ በነገው ዕለት ህዳር 22/2014 ዓ.ም የሚከበረው የአለም ኤድስ ቀን End Inequalities. End AIDS. End Pandemics በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ የሚከበር ሲሆን እንደሀገር አገልግሎቱን ለተጠቃሚዎች በእኩልነት ተደራሽ ማድረግ ወረርሽኙን መግታት በሚል መሪ ቃል ሀገራዊ አቻ ትርጉም በመስጠት በደማቅ ሁኔታ የሚከበር መሆኑ ተገልጾአል።
የመሪ ቃሉ ዋና ሀሳብ በ3 ጭብጦች ላይ ያተኮረ ሲሆን አገልግሎቱን ለተጠቃሚዎች በእኩልነት ተደራሽ ማድረግ ፤ኤችአይ ቪ ኤድስ የማህበረሰብ ጤና ችግር እንዳይሆን እንዲሁም ወቅታዊ የሆኑ እንደ ኮቪድ 19 የመሳሰሉ ወረርሽኞችን ጨምሮ በተገለሉና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ባልሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚያደርሰውን ጫና መቅረፍ ላይ የሚያተኩር ነው ሲሉ በፌደራል ኤችአይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የዘርፈብዙ ምላሽ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ክፍሌ ምትኩ ገልጸዋል።
በሀገራችን መረጃዎች እንደሚያሳዩት በአሁኑ ሰዓት 622326 የሚያክሉ ሰዎች ኤችአይ ቪ በደማቸው የሚገኝ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 480827 ያህሉ የፀረ-ኤችአይ ቪ መድሀኒት የሚወስዱ ሲሆን ይህም 77.2 ከመቶ የሆነ የአገልግሎት ሽፋን እንዳለ ያሳያል ቀሪዎቹ ከቦታ ርቀት እስከ የአገልግሎት አቅርቦት ተደራሽ ባለመሆንና ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ያሳያል።
ጽ/ቤቱ የአገልግሎት ተደራሽነት ክፍተት ከየት እንደሆነ በመለየት እና ተገቢውን ትኩረት በመስጠት የተሸለ ሆኔታ እንደፈጠር በማድረግ የዘንድሮው የአለም ኤድስ ቀን በተለያዩ ምክንያቶች ኤችአይ ቪ በደማቸው የሚገኝ አፍላ ወጣቶች እና ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ በይበልጥ የሚያተኩር ይሆናል።

Undefined
Posted on: 
Tuesday, November 30, 2021
Alarm: 
New Image: 

Add new comment