Telephone: +25111-550-34-62/33 64
Fax number: +251-11-550-40-80
Postal Code: 122326
Address: Near Bambius super market
Afewerk Building, 6th ,7th, 8th Floor,
Addis Ababa, Sub city kirkos, wereda01,
Ethiopia
የፌደራል ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት የዘርፈ ብዙ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ምላሽ ማስተባበር ዳይሬክቶሬት ለኤች አይ ቪ አጋላጭ በሆኑ ቦታዎች ለሚሰሩ ሠራተኞች የአቻ ለአቻ ውይይት መመሪያ ላይ ስልጠና ሠጠ፤
የአቻ ለአቻ ውይይት መመሪያ ፅንሰ ሀሳብ ላይ በአገር አቀፍ ደረጃ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ለሚሠሩ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር ፎካል ወይም አስተባባሪዎች ፣ በጤና ባለሙያነት ለሚያገለግሉ እና ከሠው ሀይል አስተዳደር ለተውጣጡ ባለሙያዎች ከጥር 23-25 ለሶስት ተከታታይ ቀናት በዓዳማ ሀይሌ ሪዞርት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና የተግባር ላይ ልምምድ ተካሂዷል።
ሁሉም ሠልጣኞች የአቻ ለአቻ መመሪያውን መሠረት በማድረግ ወደ ስራ ቦታቸው ሲመለሱ ፤ ከሚያከናውናቸው ተግባራት ጎን ለጎን የህይወት ክህሎት ፣ በጥልቀት ማሠብ እና ውሳኔ ሠጭነት ያለውን ጠቀሜታ ለኤች አይቪ አጋላጭ በሆኑ የስራ ቦታዎች ለሚሠሩ ሠራተኞች በቀጣይ የስራው አካል በማድረግ የኤች አይ ቪ መከላከል ስራውን ለማጠናከር የሚያግዝ የመወያያ መድረክ በመፍጠር የልምድ ልውውጥ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ።
Undefined

Posted on:
Monday, February 7, 2022
Alarm:
New Image:

Add new comment