የመንግስት አገልግሎት የመማክርት ጉባኤ ማቋቋሚያ ሰነድ ላይ ስልጠና ተሰጠ

ነሀሴ 13/2013 ዓ.ም. አዳማ ፡-የፌደራል ኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት የመንግስት አገልግሎት የመማክርት ጉባኤ ማቋቋሚያ ሰነድ ላይ እንዲሁም የአገልግሎት ማሻሻያ ጥምረት ምንነት፣ አስፈላጊነት እንዲሁም አተገባበር ላይ ያተኮረ ስልጠና ሰጠ፡፡
የጽ/ቤቱ ም/ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብረሃም ገ/መድህን ከዚህ ቀደም የጤና ልማት ሰራዊት በመባል ተግባራዊ ሲደረግ የነበረዉ ስያሜ መቀየሩንና በነበረው አተገባበር የሚነሱ ቅሬታዎችን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ጥናታዊ ዳሰሳዎችን በማድረግ በጥናቱም የተስተዋሉ ክፍተቶችን ለመፍታት የሚያስችል አዳዲስ ሀሳቦችን በማካታተትና በማዳበር አሰሪ በሆነ መልኩ መዘጋጀቱን አዉስተው የአገልግሎት ማሻሻያ ጥምረት ሲተገበር ሰራተኞች የሚያጋጥማቸውን ጫና ሁሉ ተቋቁመው ስራቸውን በአግባቡ በመወጣት ማህበረሰቡን የሚያገለግሉ እንደሆኑ የሚያግዝ ስልጠና ነው ሲሉ ስልጠናውን በከፈቱበት ወቅት ገልጸዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ደሳለኝ የስልጠናውን አላማ በገለፁበት ወቅት እንዳሉት ስልጠናው ተገልጋዮች
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል በቅንጅት የሚሰሩበትን አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
በስልጠናውም የጽ/ቤቱ ከፍተኛ ኃላፊዎችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

Undefined
የወጣበት ቀን: 
ሃሙስ, August 19, 2021
አስተዋውቅ: 

Add new comment