በህይወት ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና ለጽ/ቤቱ ሠራተኞች ተሰጣቸው

በህይወት ክህሎት ላይ ያተኮረ ስልጠና ለጽ/ቤቱ ሠራተኞች ተሰጣቸው
የካቲት 18/2013ዓ.ም በአዳማ ከተማ የተሰጠው ስልጠና ትኩረት ስላደረገበት ዋና ሃሳብ የተናገሩት አቶ ሀብታሙ ልጃለም የጽ/ቤቱ የሴቶችና ወጣቶች ማካተት ዳይሬክቶሬት ተጠባባቂ ዳይሬክተር ሰራተኞች መስሪያ ቤቱ ስለሚያከናውነው ተግባር ማወቅና መረዳት ስላለባቸው ስልጠናው ሊዘጋጅ እንደቻለ ተናግረዋል።
በዕለቱ የተሰጠውን ስልጠና በማስመልከት ንግግር ያደረጉት አቶ ክፍሌ ምትኩ የዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መስሪያ ቤቱ የጽ/ቤቱ ሰራተኞች ራሳቸውን ከኤች አይ ቪ እንዲጠብቁ የመከላከል ስራዎችን የመስራት ኃላፊነት አለበት ብለዋል።
የኤች አይቪና የስነ ተዋልዶ ጤና የህይወት ክህሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና የሰጡት አቶ ሀብታሙ ካሳ በዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስተባበር ዳይሬክቶሬት ከፍተኛ ባለሙያ ሲሆኑ የህይወት ክህሎት ላይ ትኩረት ያደረገ ማብራሪያ ለተሳታፊዎች ሰጥተዋል።በገለጻቸውም የህይወት ክህሎት አይነቶች ራስን ማወቅ፣በራስ መተማመን ፣ሀሳብን በትክክልና በአግባቡ መግለጽ፣ በጥልቀት ማሰብና ችግር የመፍታት ክህሎትን ማዳበር እንደሆነ ተናግረዋል ።አክለውም የራሱን ደካማና ጠንካራ ጎን የሚያውቅ ግለሰብ እውነት ላይ ተንተርሶ ለመኖር አይቸገርም ብለዋል።

Undefined
Posted on: 
Thursday, February 25, 2021
Alarm: 

Add new comment