የማይታይ መጠን = የተገታ መተላለፍ ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ፤

ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች፣ በጤና ባለሙያዎች የታዘዘላቸውን የጸረ-ኤችአይቪ መድኃኒት በአግባቡ በመውሰድ፣ የመድኃኒት ቁርኝቱን ሊያዛንፉ ከሚችሉ ድርጊቶች በመቆጠብ፣ በደማቸው ውስጥ የሚገኘውን የቫይረስ ቁጥር ወደ የማይታይ (በሚሊ ሊትር ከ200 ኮፒ በታች) መጠን በማድረስ፣ የጸረ-ኤችአይቪ መድኃኒታቸውን በአግባቡና ቀጣይነት ባለው መልክ በመውሰድ፣ ይህን የቫይረስ መጠን ቢያንስ ለ6 ወራትና ከዚያ በላይ በቀጣይነት ባለበት እንዲቆይ ማድረግ ከቻሉ፣ በኤችአይቪ ላልተያዘ የትዳር ወይም የወሲብ አጋራቸው ቫይረሱን የማስተላለፍ ዕድላቸው የተገታ መተላለፍ ይሆናል፡፡
የተገታ መተላለፍ ላይ ለመድረስ በርካታ ስራ የሚፈልግ ሲሆን እነሱም የቫይረስ መጠን ልኬት ፍላጎትን መጨመር፣ የጸረ-ኤችአይቪ መድኃኒት ቁርኝትን ማሻሻል፣ የጤና ስርዓት ማሻሻል፣ ጥምር የኤችአይቪ መከላከል ሥራ ማጠናከርና የኤችአይቪ ምክርና ምርመራን ማጠናከር ናቸው። የጸረ-ኤችአይቪ ህክምና የሚያስገኘውን ጥቅም በመረዳትና በተለይም ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች ላይ የሚደርሰውን መድሎና መገለልን በማስቀረት ኤችአይቪ በደማቸው መኖሩን ያላወቁ ሰዎች፣ በምርመራ ራሳቸውን እንዲያውቁ የሚደረገውን የማስተማር፣ የምክርና የምርመራ አገልግሎት ማጠናከር፣ የ=የ ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ናቸው። ጽንሰ ሀሳቡን በጥንቃቄና በሚገባ በመረዳት፣ ኤችአይቪ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች፣ መድሀኒታቸውን በሐኪም ትዕዛዝ መሰረት በትክክል በመውሰድ፣ በዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ፣ የጤና ባለሙያዎችና የሌሎች ባለድርሻ አካላትና የአጋር ድርጅቶች፣ የመላው ማህበረሰብን የላቀ ተሳትፎ ይጠይቃል፡፡
ይህ ፕሮግራም በ98 የዓለም ሀገሮች ተግባራዊ የሆነና 25 ሀገሮችም ሀገረኛ አቻ ስያሜ ሰጥተውት ተጨባጭ ውጤቶች ያስገኘ ነው። በሀገራችንም የሚታየውን ማግለል እና መድሎ በማስወድ እና የኤችአይቪ ስርጭቱን በመግታት ሀገራችን እ.ኤ.አ. በ2030 ላቀደችው ከኤድስ ነጻ የሆነች ሀገር መደላድል ይፈጥራል።

Undefined
Posted on: 
Tuesday, March 23, 2021
Alarm: 

Add new comment