ኤችአይቪ አስጊና ትኩረት የሚሻ ቢሆንም በቂ ትኩረት አለማግኘቱ ተገለጸ።

Undefined

ኤችአይቪ የስርጭት ምጣኔው አስጊና ልዩ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ቢሆንም የከፍተኛ አመራሩም ሆነ የሌሎች ባለድርሻ አካላት ትኩረትን አሁንም በሚፈለገው ልክ አለማግኘቱ የተገለጸው ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ መካሄድ በጀመረው የ5 አመት የስትራቴጂክ እቅድ ማስተዋወቂያና የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም መገምገሚያ መድረክ ላይ ነው ፡፡
ከ2014-2018 ዓ.ም ተግባራዊ የሚሆነው ስትራቴጂክ እቅድ ከሌላው ጊዜ በተለየ የስርጭት ምጣኔው ከፍተኛ የሆነበትን አካባቢና ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦችን በመለየትና እንደየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ፣ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ፣ ፍትሐዊ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ፣ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ከመቼውም በላይ ለማስፋት፣ታላሚ አድርጎ የተዘጋጀ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህንን ወደተግባር መቀየር የሁሉም የቤት ስራ ሊሆን እንደሚገባ ተገለጿል።

Posted on: 
Wednesday, April 7, 2021
Alarm: 

Add new comment