የአዲሱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ትውውቅ

Undefined

የፌደራል ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ፅ/ቤት ከክልል ጤና ቢሮ እና ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከ.መቆ. ፅ/ቤት ለተውጣጡ የዕቅድ ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እና የዘርፈ ብዙ ምላሽ ማስተባበር የፕሮግራም አስተባባሪዎች በቀጣይ አምስት አመት ተግባራዊ የሚደረገውን አገር አቀፍ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ስትራቴጂክ እቅድ በቢሾፍቱ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
የፅ/ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ገ/መድህን ከ2014-2018 ዓ.ም. ተግባራዊ የሚደረገውን ስትራቴጂክ ሁሉም ኤች አይ ቪን በመከላከሉ ዙሪያ የሚሰራ ከከፍተኛ አመራሩ እስከ ባለሙያው በጥልቀት በመረዳት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀው፤ ስትራቴጂክ እቅዱ በጣም የተዋጣለት እና ሁሉን አቀፍ ምላሽ እሚሰጥ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው ገልፀዋል።
ስትራቴጂክ እቅዱን የማስተዋወቅ ፕሮግራም ከመጋቢት 12-15 በደብረ ብረሃን ከተማ ተካሂዶ እንደነበር ይታወቃል።

Posted on: 
Wednesday, April 21, 2021
Alarm: 

Add new comment