ሚዲያ ተቋማት ላይ ሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች በጤና ዘገባ (Health reporting) ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ሚያዝያ 18/2013 ዓ.ም አዳማ፦ የሚዲያ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች በጤና ዘገባ (Health reporting) ያለዉን ክፍተት ለመቅረፍ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በፌደራል ኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት እና በCDC ኢትዮጲያ ትብብር ተሰጠ።
ስልጠናውን ለሚዲያ ባለሙያዎች የሰጡት በCDC የኮሙኒኬሽን ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዮናታን አለሙ እንዳሉት “አንድ ጋዜጠኛ ስለጤና በሚዘግብበት ወቅት ዋናው አላማው መሆን ያለበት ማህበረሰቡ ጋር የነበረ አላስፈላጊ የሆነ ባህሪ መቀየር ፣በቀየርነው የቀድሞው ባህሪ ምትክ ሌላ አዲስ የሆነ ባህሪን እንዲያዳበር ማድረግ እና አዲስ የተተካውን ባህሪ ማህበረሰቡ አጠናክሮ እንዲቀጥል ማድረግ ነው ብለዋል።” አክለውም በጤና ዘገባ ወቅት ዘገባው ከመሰራቱ በፊት አስፈላጊው የሆነ ጥናት እና በሙያው በቂ የሆና ዕውቀት ያላቸውን ባለሙያዎች ስለጉዳዩ ማነጋገር እንዳለባቸው ገልፀዋል።
የማህበረሰብ ጤና ባለሙያ የሆኑት አቶ እስማኤል አህመድ ለሚዲያ ባለሙያዎች የማታይ መጠን = ¬የተገታ መተላለፍን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ አንድ ሰው የማይታይ መጠን= የተገታ መተላለፍ ደረጃ ላይ ሊደርስ የሚችለው የጸረ-ኤች አይቪ/ኤድስ መድሐኒቱን ሐኪም በሚያዘው መሰረት በአግባቡ በመውሰድ በደማቸው ውሰጥ የሚገኘውን የቫይረስ መጠን መቀነስ ሲችሉ ብቻ መሆኑን አስረድተዋል። በተጨማሪም በደማቸው ውስጥ ያለውን የቫይረስ መጠን መቀነሳቸው የትዳር አጋራቸውን እንዲሁም ሌሎች የቤተሰብ አባሎቻቸውን ከቫይረሱ ለመጠበቅ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልፀዋል።

Undefined
Posted on: 
Tuesday, April 27, 2021
Alarm: 

Add new comment