ለጽ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች በሰው ሀብት ህጎች ላይ ስልጠና ተሰጠ

Undefined

ሰኔ 17/2013ዓ.ም ደብረብርሀን:— ለፌደራል ኤችአይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አመራሮችና ሠራተኞች በሰዉ ሀብት ሕጎች ፣አዋጅ እና ደንብ ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ።

የጽ/ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ገ/መድህን በመክፈቻ ንግግራቸዉ እንዲህ አይነት የስልጠና መድረክ መዘጋጀቱ አመራሩና ሠራተኛው መብትና ግዴታውን ለማወቅ ያግዘዋል። ይህ መሆኑ ለተቋሙም ሆነ ለግለሰቡ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸው፣ ሰራተኛውም ደንቦቹንና ህጎቹን በማወቅ ግዴታውን እንዲወጣና መብቱን እንዲያስከብር አሳስበዋል።

የጽ/ቤቱ የሠው ሀብት ስራ አመራር እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ይሄነዉ ብርሃኔ ሰራተኞቻችን በጽ/ቤቱ በሚኖራቸው ቆይታ ስለሚኖራቸው መብት እና ግዴታ እንዲሁም ፣በፌደራል የመንግስት ሠራተኞች አዋጅ ምንነትና አተገባበር ዙሪያ ስልጠና መዘጋጀቱ መብቱን ያወቀና ግዴታው ሊወጣ የሚችል ብቁ ሰራተኛ እንዲሆን የሚያስችል ትልቅ ጠቀሜታ ያለው ስልጠና እንደሆነ ገልጸዋል።

ስልጠናዉን ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በመጡ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በቀረቡት ሰነዶች ላይ ዉይይት ተደርጓአል።

Posted on: 
Thursday, June 24, 2021
Alarm: 
New Image: 

Add new comment